Zechariah 13

ከኀጢአት መንጻት

1“በዚያ ቀን የዳዊትን ቤትና የኢየሩሳሌምን ነዋሪዎች ከኀጢአትና ከርኩሰት የሚያነጻ ምንጭ ይከፈታል።

2“በዚያ ቀን የጣዖታትን ስም ከምድሪቱ አጠፋለሁ፤ ከእንግዲህም አይታሰቡም” ይላል እግዚአብሔር ጸባኦት። “ነቢያትንና ርኩስ መንፈስን ከምድሪቱ አስወግዳለሁ። 3ማንም ትንቢት ቢናገር ወላጅ አባትና እናቱ፣ ‘በእግዚአብሔር ስም ሐሰት ተናግረሃልና ሞት ይገባሃል’ ይሉታል። ትንቢት ሲናገርም የገዛ ወላጆቹ ይወጉታል።

4“በዚያን ቀን እያንዳንዱ ነቢይ ስለሚናገረው የትንቢት ራእይ ያፍራል፤ ለማታለልም የነቢያትን ጠጕራም ልብስ አይለብስም። 5እርሱም፣ ‘እኔ ገበሬ እንጂ ነቢይ አይደለሁም፤ ከልጅነቴ
ወይም ዐራሽ፤ በወጣትነቴ የተሸጥሁ ሰው
ጀምሮ ኑሮዬ የተመሠረተውም በዕርሻ ላይ ነው’ ይላል።
6አንድ ሰው፣ ‘ይህ በሰውነትህ
በእጆችህ መኻል ያሉ ቍሰሎች የሚሉ አሉ።
ላይ ያለው ቍስል ምንድን ነው?’ ብሎ ቢጠይቀው፣ ‘በባልንጀሮቼ ቤት ሳለሁ የቈሰልሁት ነው’ ይላል።”

እረኛው ተመታ፤ በጎቹ ተበተኑ

7 እግዚአብሔር ጸባኦት እንዲህ ይላል፤
“ሰይፍ ሆይ፤ በእረኛዬ፣
በቅርብ ወዳጄ ላይ ንቃ!
እረኛውን ምታ፣
በጎቹ ይበተናሉ፤
እኔም ክንዴን ወደ ታናናሾቹ አዞራለሁ።”
8 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “የምድር ሁሉ፣
ሁለት ሦስተኛው ተመትቶ ይጠፋል፤
አንድ ሦስተኛው ግን በውስጡ ይቀራል፤
9ይህን አንድ ሦስተኛውን ክፍል ወደ እሳት አመጣለሁ፤
እንደ ብር አነጥራቸዋለሁ፤
እንደ ወርቅም እፈትናቸዋለሁ፤
እነርሱ ስሜን ይጠራሉ፤
እኔም እመልስላቸዋለሁ፤
እኔም፣ ‘ሕዝቤ ናቸው’ እላለሁ፤
እነርሱም፣ ‘እግዚአብሔር አምላካችን ነው’ ይላሉ።”
Copyright information for AmhNASV